EthiopiaNews

ከሰሞኑ በጋምቤላ ከተማ በተከሰተ የፀጥታ መደፍረስና ጥቃት ቀጥተኛ ተሳትፎ፣ ማስተባበር እና ትብብር የነበራቸው የፖሊስ አባላትን ጨምሮ በርካታ ግለሰቦች በሕግ ቁጥጥር ሥር መዋላቸው የክልሉ ፖሊስ አስታውቋል።

ፖሊስ እንዳስታወቀው የፀጥታ ግብረ ኃይሉ ባካሄደው ዘመቻ የጦር መሣሪያዎች የተያዙ ሲሆን፣ በአሁኑ ወቅት በከተማዋ ሰላምና መረጋጋት በመስፈኑ ሕብረተሰቡ በነፃነት መንቀሳቀስ እንደሚችል ተገልጿል።

የከተማውን ሰላም ይበልጥ ለማስጠበቅ የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ እስከ ምሽቱ 1፡00 ሰዓት ብቻ እንዲሆን ገደብ መጣሉን እና የሕግ ማስከበር ሥራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተመላክቷል።