EthiopiaNews

የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር መስከረም 5/2018 ዓ.ም በተጀመረው ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት የመመለስ ስራ እስካሁን ከ111 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገር ቤት መመለሳቸውን አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ ይሄን ያለው በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 1ሺህ 561 ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ነው።

በሳምንቱ ውስጥ በተደረገ 7 ዙር በረራ የተመለሱት 929 ወንዶች፣ 580 ሴቶች እና 52 ህፃናት ሲሆኑ ከተመላሾች መካከል 99 እድሜያቸው ከአስራ ስምንት አመት በታች የሆኑ ታዳጊዎች ይገኙበታል።

ሚኒስቴሩ ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ በማድረግ ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራም እየተሰራ መሆኑን ገልጿል፡፡