EthiopiaNews

ራያ ዩኒቨርሲቲ ከዛሬ ጥቅምት 16 ቀን 2019 ዓ.ም ጀምሮ ነባር ተማሪዎችን መቀበል መጀመሩን አስታወቀ።

ተማሪዎቹ በክልሉ በተፈጠረ የጸጥታ ችግር ምክንያት በሌሎች አካባቢዎች በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ተመድበው የነበሩ ሲሆን አሁን ግን ወደ ዩኒቨርስቲው መመለስ መጀመራቸው ተገልጿል።

ዩኒቨርሲቲው ከ2 ሺህ በላይ ነባር ተማሪዎችን እንደሚቀበል የገለጸ ሲሆን ከ3 ሺህ በላይ አዳዲስ ተማሪዎችን ለመቀበል ዝግጅት ማድረጉን አስታውቋል።

ተማሪዎች ያለ ምንም የጸጥታ ስጋት ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ከጸጥታ አካላት እና ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር ከፍተኛ ዝግጅት መደረጉም ተጠቁሟል።