ኢትዮጵያ እና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ወታደራዊ ትብብራቸውን ይበልጥ ለማጠናከር መስማማታቸውን የኢትዮጵያ መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል።
የመከላከያ ሚኒስትር መሐመድ እድሪስ ከኤምሬቶች አምባሳደር አብደላ ሀሰን አልሻምሲ ጋር ባደረጉት ውይይት እዚህ ስምምነት ላይ መደረሱም ተገልጿል፡፡
አምባሳደር አልሻምሲ ሀገራቸው ከኢትዮጵያ ጋር ያላት ስትራቴጂያዊ አጋርነት ይበልጥ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ፍላጎት እንዳላትም ጠቅሰዋል።
በውይይቱ ሀገራቱ በጋራ ብሔራዊ ጥቅሞቻቸው ላይ የተመሠረተ ጠንካራ የሁለትዮሽ ወዳጅነት የገነቡ መሆኑ ተጠቁሞ ይህንን አጋርነት ወደ ላቀ እና ዘላቂ የወታደራዊ ትብብር ደረጃ ለማሸጋገር በቁርጠኝነት ለመስራት መስማማታቸውም ተገልጿል።
