InternationalNews

በእስራኤል በተካሄደው ጠቅላላ ምርጫ እስካሁን ድረስ አሸናፊው አለመለየቱ ተነገረ፡፡

እስካሁን ድረስ በተቆጠረው ግማሽ ያህል የመራጮች ድምፅ ውጤት መሰረት የኔታንያሁ ሊኩድ ፓርቲም ሆነ የተቀናቃኙ ኤሴንኮት ያሻር ፓርቲ በሀገሪቱ ፓርላማ አብላጫ ድምፅ ማግኘት የሚያስችላቸውን ውጤት ማግኘት አልቻሉም፡፡

ያሻር ፓርቲ በርካታ ተፎካካሪ ፓርቲዎችን በአንድ አጣምሮ የተቋቋመ እና የጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁን ሊኩድ ፓርቲ ከመገዳደር ባለፈ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የስልጣን ዘመን እንዲያበቃ እየሰራ የሚገኝ ነው ተብሏል፡፡

ኔታንያሁ ጠንካራ ቀኝ ዘመም መንግስት በእስራኤል መፈጠር አለበት ሲሉ ተቀናቃኛቸው ኤሴንኮት ደግሞ እስራኤላውያን የኔታንያሁ የስልጣን ዘመን እንዲያበቃ ድምፃቸውን መስጠት አለባቸው ሲሉ ለደጋፊዎቻቸው ተናግረዋል፡፡

እስካሁን በተቆጠረው የመራጮች ድምጽ ጠቅላይ ሚኒስትር ኔታንያሁ በተቀናቃኛቸው ጋዲ ኤስንኮት ላይ ጠባብ የሆነ ብልጫ አላቸው ተብሏል።