ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በብራዚል ምርጫ የተሸነፉት ፍላቪዮ ቦልሶናሮ ወደ አሜሪካ እንዲመጡ ማድረጋቸውን ገለፁ፡፡
እሁድ በተካሄደው የብራዚል ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ በሉላ ዳሲልቫ ሽንፈት የደረሰባቸው ቦልሶናሮ ከነቤተሰቦቻቸው ወደ አሜሪካ እንዲገቡ የአሜሪካ ውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ቪዛ መስጠቱ ነው የተሰማው፡፡
ትራምፕ ቦልሶናሮ በብራዚል ምርጫ እንዲያሸንፉ ከመፈለግ ባለፈ የተለያዩ ጥረቶችን ሲያደርጉ እንደነበረ የሚነገር ሲሆን ፕሬዝዳንቱ የብራዚሉ የምርጫ ውጤት እንግዳ እንደሆነባቸውም ተናግረዋል፡፡
በብራዚል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፓስፖርታቸውን ለሀገሪቱ መንግሰት እንዲያስረክቡ የተጠየቁት ቦልሶናሮ እምቢታን በመምረጥ ወደ አርጀንቲና ከሸሹ በኋላ ከአርጀንቲና ወደ አሜሪካ መግባታቸው ነው የተሰማው፡፡
