ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ኢትዮጵያ ዛሬ የመጀመሪያዎቹን አስራ ሁለት የሱ-35 4ኛ++ ትውልድ የጦር ጄቶች መረከቧን እና 4 የኤስ-400 የአየር መከላከያ ባትሪዎችን ልትረከብ መሆኑን ተናገሩ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይሄን ያሉት ዛሬ በተጀመረው 3ኛው የሩሲያ -አፍሪካ ጉባዔን ለመታደም ሞስኮ ባሉበት ጊዜ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያን ሰላምና ደህንነት በዘላቂነት ለማረጋገጥ የምናደርገው ሁለንተናዊ ጥረት ዛሬ ሌላ አዲስ ምዕራፍ ላይ ደርሷል ብለዋል።
ኢትዮጵያ በመከላከያ ኃይል እያደረገች ያለው ዝግጁነት ጥቃትን ቀድሞ ማስቀረት የሚያስችላትን አቅም እያላበሳት እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልፀዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከዚህ ቀደም ከሩሲያ መንግስት ጋር በደረስነው ስምምነት መሰረት ዛሬ የመጀመሪያዎቹን አስራ ሁለት የሱ-35 4ኛ++ ትውልድ የጦር ጄቶች መርከቧን እና አራት የኤስ-400 የአየር መከላከያ ስርዓት ባትሪዎችን ልትረከብ ነው ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ከስምምነታችን አንድ ዓመት አስቀድሞ እነዚህን የጦር አውሮፕላኖች እንድንረከብ ስላሳዩት ትጋት አመሰግናለሁ ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ እነዚህን የጦር ጄቶች በመታጠቅ ኢትዮጵያ ከሰሃራ በታች ካሉ የአፍሪካ ሀገራት ቀዳሚ ሆናለች ብለዋል።
ይህ ታሪካዊ ስኬት የሀገራችንን ሉዓላዊነት ይበልጥ የሚያጠናክር እንደሆነ የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደፊትም የጋራ ደህንነታችንን እና ቀጣናዊ መረጋጋትን ለማረጋገጥ የምናደርገውን ጉዞ በልበ ሙሉነት እንድንቀጥል ትልቅ አቅም ይሆነናል ብለዋል።
