EthiopiaNews

ትምህርት ሚኒስቴር በፌዴራል ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የመግቢያ ፈተና ወስደው ያለፉ ተማሪዎች የተመደቡበትን ትምህርት ቤት እንዲያረጋግጡና የኦንላይን ምዝገባቸውን እንዲያጠናቅቁ አሳስቧል።

ሚኒስቴሩ ባወጣው መረጃ ተማሪዎች የኦንላይን ምዝገባቸውን ሙሉ በሙሉ ካጠናቀቁ በኋላ እስከ መጪው እሁድ ጥቅምት 22 ቀን 2019 ዓ.ም ድረስ ወደ ተመደቡበት ትምህርት ቤት ገብተው ትምህርታቸውን መጀመር እንዳለባቸውም ገልጿል።

ይህ ጥሪ የቀረበው በፌዴራል ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ባሉ ክፍት ቦታዎች ላይ ተማሪዎችን ለመቀበል በወጣው ማስታወቂያ መሠረት ፈተና ወስደው ማለፍ ለቻሉ ተማሪዎች እንደሆነም ተጠቁሟል።