የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ የባንክ ሂሳባቸውን ከፋይዳ መታወቂያቸው ጋር ያላስተሳሰሩ ደንበኞች እስከ መጪው ጥቅምት 30 ድረስ እንዲያስተሳስሩ አሳሰበ፡፡
እስካሁን ሂሳባቸውን ከፋይዳ መታወቂያ ጋር ባለማስተሳሰራቸው ምክንያት ሂሳባቸው የታገደ ደንበኞች ይህንኑ በማድረግ በሂሳባቸው ላይ የተጣለውን እግድ እንዲያስነሱም ጠይቋል፡፡
ደንበኞች የፋይዳ መታወቂያ ቁጥራቸውን ይዘው በባንኩ ቅርንጫፎች በመገኘት ወይም ባሉበት ሆነው በበይነ መረብ እንዲያስተሳስሩም ባንኩ ጥሪ አቅርቧል፡፡
በሌላ በኩል ባንኩ አጠቃላይ ሀብቱ 3 ነጥብ 16 ትሪሊዮን ብር እንዲሁም ካፒታሉ ደግሞ 224 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር መድረሱን ይፋ አድርጓል።
በአሁኑ ወቅት 1 ሺህ 916 ቅርንጫፎች ያሉት ባንኩ አጠቃላይ የደንበኞች ቁጥር ደግሞ 48 ነጥብ 1 ሚሊዮን እንዲሁም የሞባይል ባንኪንግ ተጠቃሚዎች ቁጥር ከ11 ሚሊዮን በላይ መድረሱንም ጠቅሷል፡፡
