InternationalNews

ከዚህ ቀደም ቪዛን ያለአግባብ የተጠቀሙ ወይም ወደፊት ያለአግባብ ለመጠቀም የሚሞክሩ ግለሰቦችና ቤተሰቦቻቸው አዲስ ቪዛ ማግኘት እንደማይችሉ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ገለጹ።

አምባሳደሩ የቪዛ አጠቃቀምን በተመለከተ ለተጓዦች ባስተላለፉት ጥብቅ ማሳሰቢያ አሜሪካ የኢሚግሬሽን ሕጎቿን በጥብቅ እየተገበረች መሆኑን ገልጸዋል።

አምባሳደሩ ባስተላለፉት መልእክት የአሜሪካ ቪዛ የማግኘት ዕድል መብት አለመሆኑን ገልጸው ተጠቃሚዎች የተሰጣቸውን ቪዛ በትክክለኛው ዓላማና መንገድ ብቻ ሊጠቀሙበት እንደሚገባም አሳስበዋል።