EthiopiaNews

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ከፕሬዚዳንት ፑቲን ጋር በኢትዮጵያና በሩሲያ መካከል ያለውን የቆየ ግንኙነት ይበልጥ ማጠናከር በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ ፍሬያማ የሁለትዮሽ ውይይት ማካሄዳቸውን ተናገሩ።

ውይይታቸው በኒውክሌር ኃይል፣ በጤናና ንግድ ዘርፎች ያለውን ትብብር እንዲሁም በጋራ ፍላጎት ላይ የተመሰረቱ የሁለትዮሽ እና የባለብዙ ወገን ጉዳዮችን ያካተተ እንደነበረም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለውይይት፣ ለጋራ መግባባት እና ለኢትዮጵያ-ሩሲያ ግንኙነት ቀጣይነት ያለው እድገት ያለንን የጋራ ቁርጠኝነት የሚያሳየውን የመደመር መጽሐፌን የሩሲያኛ ዕትም ለፕሬዚዳንት ፑቲን አበርክቼላቸዋለሁ ብለዋል።