የትግራይ መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ” በአዲስ ስያሜ ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን ፈቃድ አግኝቷል።
ባለስልጣን መ/ቤቱ ይሄን ያለው የትግራይ ቴሌቪዥንን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ነው።
ቀደም ሲል ታግዶ የነበረው “የትግራይ መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ” የትግራይ ሚዲያ ኮርፖሬሽን በሚል አዲስ ስያሜ ነው በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የብሮድካስት ፈቃድ የተሰጠው።
የትግራይ መገናኛ ብዙኃን ኤጀንሲ ከመገናኛ ብዙኃን አዋጅ ጋር የሚቃረኑ ይዘቶችን በማሰራጨቱ ምክንያት ፈቃዱ ተሰርዞ የነበረ መሆኑን ባለስልጣኑ አስታውሷል።
ሆኖም የትግራይ ክልል ባለአደራ አስተዳደር ኤጀንሲው የክልሉን ሰላምና መረጋጋት ለማረጋገጥና የሕዝብ ድምፅ በመሆን አዎንታዊ አስተዋጽኦ እንዲያበረክት በሚል የስያሜ ለውጥ በማድረግ እንዲፈቀድለት ጥያቄ በማቅረቡ በአዲሱ ስያሜ ፈቃዱ እንደተሰጠም ነው የጠቀሰው፡፡
የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ለብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽኑ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለሥልጣን ጥሪ አቅርቧል።
መረጃው ከኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የተገኘ ነው።
