EthiopiaNews

የማዕከላዊ ኢትዮጵያ የስምጥ ሸለቆ ጂኦፓርክ በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) የዓለም ጂኦፓርኮች ዝርዝር ውስጥ በመካተት ዓለም አቀፍ እውቅና አገኘ።

በ11ኛው የዩኔስኮ ዓለም አቀፍ ጂኦፓርኮች ካውንስል መደበኛ ስብሰባ ላይ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ስምጥ ሸለቆ ጂኦፓርክ የዩኔስኮ ዓለም አቀፍ ጂኦፓርክነት እውቅና እንዲያገኝ በይፋ መፅደቁን ነው የባሕል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር ያስታወቀው።

ሚኒስቴሩ ይህ ታሪካዊ ስኬት ኢትዮጵያ ከሞሮኮ፣ ታንዛኒያና ቱኒዚያ በመቀጠል የዩኔስኮ ዓለም አቀፍ ጂኦፓርክ እውቅና ያገኘች አራተኛዋ የአፍሪካ ሀገር እንድትሆን አስችሏታል ብሏል።

ኢትዮጵያ ይህንኑ ስኬት የሚያረጋግጠውን ይፋዊ የእውቅና ሰርተፍኬት ሚያዚያ 19 2019 አ.ም በይፋ ትረከባለች ተብሎ እንደሚጠበቅ ሚኒስቴሩ ገልጿል።

ይህ ዕውቅና ኢትዮጵያ በሚዳሰሱና በማይዳሰሱ የዓለም ቅርሶቿ፣ በጥንታዊ የጽሑፍ ቅርሶቿና በመካነ ብዝኃ ሕይወት ሀብቷ ከምትታወቅበት የተፈጥሮ፣የታሪክና የባህል ቅርስ ሀብት ባሻገር፣ በጂኦፓርክና በጂኦ-ቱሪዝም ዘርፍም አዲስ ምዕራፍ እንድትከፍት ዕድል ይፈጥራል።

በተለይም የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ስምጥ ሸለቆ የዩኔስኮ ዓለም አቀፍ ጂኦፓርክነት እውቅና ማግኘት በኢትዮጵያ የቱሪዝም ታሪክ ውስጥ አዲስና ታላቅ ምዕራፍ እንደሚከፍት ተገልጿል።