የአፍሪካ ልማት ባንክ ለኢትዮጵያና ጅቡቲ ከፀሃይ ሃይል ኤሌክትሪክ ማመንጫ ፕሮጀክት 50 በመቶ ወጪ ይሸፍናል ተብሏል።
ይህ የተገለጸው የአፍሪካ ልማት ባንክ ቡድን ኢትዮጵያና ጂቡቲ ከፀሃይ ሃይል ኤሌክትሪክ ማመንጫ ፕሮጀክት ፖርትፎሊዮ መነሻ ሃሳብ ላይ በዘርፉ ባሉ አስቻይ የህግ ማዕቀፎች ዙሪያ ከኢነርጂ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ባህሩ ኦሊጂራ ጋር ባደረጉት ውይይት ነው፡፡
በአፍሪካ ልማት ባንክና በሌሎች የፋይናንስ ተቋማት ድጋፍ ተግባራዊ እንዲደረግ የታቀደው ፕሮጀክቱ በኢትዮጵያና ጂቡቲ ሲሆን በጅቡቲ 50 ሜ.ዋት፣በኢትዮጵያ 125 ሜ.ዋት አቅም ያለው ሶላር ሃይል ማመንጫ ለመገንባት ታሳቢ የተደረገ ነው ተብሏል።
በባንኩ 57 በመቶ ወጪ የሚሸፈን ሲሆን ቀሪው ከሌሎች ፈይናንስ ተቋማት ለማግኘት የታቀደ መሆኑን ከነዳጅና ኤነርጂ ባለስልጣን የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
