EthiopiaNews

የኢሰመኮ ዋና ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ኤርቪን ማሲንጋ ጋር በኢትዮጵያ የሰአብዊ መብቶች ሁኔታ ዙሪያ ተወያይተዋል።

በዋና መስሪያ ቤት አምባሳደሩን ተቀብለው ያነጋገሩት ዋና ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ሁኔታ እና በጋራ ፍላጎቶች ላይ ያተኮረ ሰፊ እና ገንቢ ውይይት ማድጋቸውን ገልፀዋል።

ዋና ኮሚሽነሩ ለአምባሳደሩ የኮሚሽኑን የቅርብ ጊዜ ግኝቶች እና ይፋዊ መግለጫዎች በቀድሞው አርሲ ዞን የተፈጸሙ የሰብአዊ መብት ጥሰቶችን አስመልክቶ ምርመራ ጨምሮ ገለጻ ማድጋቸውን ተናግረዋል።

በተጨማሪም በሀገሪቱ ባሉ አጠቃላይ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታዎች ላይ መወያየታቸውን የገለፁት ዋና ኮሚሽነሩ፣ እስካሁን በተስተዋሉ ችግሮች በተመዘገቡ ውጤቶች እና ዜጎችን ለመጠበቅና ተጠያቂነትን ለማስፈን ዘላቂ ጥረት ማድረግ ስላለው አስፈላጊነት ሀሳብ መለዋወጣቸውን ገልፀዋል።

በውይይቱ በኢሰመኮ እና በአሜሪካ ኤምባሲ መካከል ያለውን ትብብር ለማጠናከር፣ በተለይም የተቋማት አቅምን በማጎልበት፣ የሕግ የበላይነትን  በማረጋገጥ እና የሰብአዊ መብት ጥበቃን በማስፋፋት በኩል ባሉ እድሎች ላይ መክረዋል።