EthiopiaNews

የኬንያው ሳፋሪኮም ኩባንያ በኢትዮጵያ ቅርንጫፉ ላይ ሲያጋጥመው የነበረው የካፒታል ወጪ በ53 በመቶ መቀነሱን አስታወቀ።

ኩባንያው በኢትዮጵያና በኬንያ ገበያ ያሳየውን የተሻሻለ አፈጻጸም ተከትሎም እስከ መስከረም ወር መጨረሻ በነበሩት ስድስት ወራት ከታክስ እና ከወለድ በፊት ያለው አጠቃላይ የኩባንያው ገቢ በ40 በመቶ ማደጉንም ገልጿል፡፡

በዚህ ጊዜ ውስጥ አጠቃላይ የኩባንያው ገቢ 701 ሚሊዮን ዶላር የደረሰ ሲሆን፣ ይህም ባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ከተመዘገበው 502 ሚሊዮን ዶላር ብልጫ ያለው መሆኑን ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

በኢትዮጵያ ከ15 ሚሊዮን በላይ ደንበኞች ያሉት ሳፋሪኮም በእዚህ ጊዜ ውስጥ 87 ሚሊዮን ዶላር የካፒታል ወጪ ያወጣ ሲሆን ይህም ከአንድ ዓመት በፊት ከነበረው የ187 ሚሊዮን ዶላር ያነሰ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡