የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከ3 ነጥበ 1 ትሪሊዮን ብር በላይ ሀብት እንዳለውና ይህም ከምሥራቅ አፍሪካ ቀዳሚው ባንክ እንደሚያደርገው ገለፀ።
ባንኩ በ2018 በጀት ዓመት 3 ነጥብ 48 ቢሊዮን ግብይቶችን በዲጂታል አማራጮቹ በማስተናገድ ከ22 ትሪሊዮን ብር በላይ ጠቅላላ ግብይት ማከናወኑን ጠቁሟል።
በዚህም ከአጠቃላይ ሀገራዊ ዲጂታል ግብይት 73 በመቶ የሚሆነው ድርሻ መያዙ ነው የገለጸው።
ይህ እንዳለ ሆኖ የባንኩ ሠራተኞች በስነምግባር ታንፀው፣ የደንበኛ አገልግሎትን በላቀ ደረጃ በማስቀጠል ባንኩ የተጣለበትን ሀገራዊ ኃላፊነት በአግባቡ እንዲወጣ ማስቻል እንደሚኖርባቸው ጥሪ አቅርቧል፡፡
