የገንዘብ ሚኒስቴር ኢትዮጵያ በፈረንጆቹ 2024/25 የበጀት ዓመት ከልማት አጋር አካላት 7.6 ቢሊየን ዶላር ማግኘቷን አስታውቋል።
ሚኒስቴሩ ይሄን ያለው አዲስ ባወጣው ዝርዝር ሪፖርት ላይ ነው።
ኢትዮጵያ ድጋፉን ያገኘችው የአለም የገንዘብ ድርጅት እና የአለም ባንክን ጨምሮ ከ17 የልማት አጋር አካላት መሆኑ በሪፖርቱ ተገልጿል።
ኢትዮጵያ በዚሁ አመት ካገኘችው 7.6 ቢሊየን ዶላር ድጋፍ ውስጥ 67 ነጥብ 4 በመቶ በብድር እና ቀሪው 32 ነጥብ 5 በመቶ በድጋፍ መልክ ነው ተብሏል።
ከልማት አጋር አካላት የተገኘው ድጋፍ ኢኮኖሚውን ለማረጋጋት እና የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን ለመደገፍ እንደዋለ ሪፖርቱ አመልክቷል።
መረጃው ከገንዘብ ሚኒስቴር የተገኘ ነው።
