አዲግራት ዩኒቨርሲቲ በክልሉ በተፈጠረው ሁኔታ ምክንያት ለጊዜው በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ተመድበው የነበሩ ተማሪዎቹን መቀበል ጀመረ።
ዩኒቨርሲቲው ይሄን ያለው ባወጣው መግለጫ ነው።
ዩኒቨርሲቲው በሌሎች ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተመድበው የነበሩ ተማሪዎች ወደ ቀድሞ የትምህርት ተቋማቸው ለመመለስ ያቀረቡትን ጥያቄ ተቀብሎ የምዝገባ ቀኑን ማራዘሙን ጠቁሟል።
ዩኒቨርሲቲው ትናንት ጀምሮ በመጀመሪያው ዙር ወደ ዩኒቨርሲቲው በርካታ ተማሪዎችን መቀበሉን ገልፆ ዛሬ እና ነገ በተለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተመድበው የቆዩ ተማሪዎች ወደ ግቢው እንደሚገቡ አስታውቋል።
መረጃው ከአዲግራት ዩኒቨርሲቲ የተገኘ ነው።
