የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ዛሬ ባካሄደው የ140 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ጨረታ አንዱን ዶላር በ159 ብር ከ70 ሳንቲም መሸጡን አስታወቀ።
ባንኩ በዛሬው ዕለት ያካሄደውን ጨረታ በተመለከተ ባወጣው መግለጫ 31 ባንኮች ተሳትፈው 26ቱ አሸናፊ መሆናቸውን ነው ያስታወቀው።
በዛሬው ጨረታ 156 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ፍላጎት በባንኮች መታየቱም ነው የተገለጸው፡፡
ብሔራዊ ባንክ ከሁለት ሳምንት በፊት ባደረገው የ140 ሚሊየን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ጨረታ አንዱን ዶላር በተመሳሳይ በ159 ብር ከ70 ሳንቲም መሸጡ ይታወሳል።
