EthiopiaInternationalNews

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከቱርኩ ፕሬዝዳንት ሬሲኘ ጣይብ ኤርዶጋን ጋር የሁለትዮሽ ውይይት ማድረጋቸውን ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት በCOP31 የመሪዎች ጉባኤ ዋዜማ በአንታሊያ ቱርክ በመገኘት ከቱርኩ ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን ጋር ፍሬያማ ውይይት አድርገናል ብለዋል።

በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ጠንካራ አጋርነት መሠረት በማድረግ፣ የሁለትዮሽ ትብብራችንን የበለጠ ማጠናከር በሚቻልባቸው ዕድሎች ላይ ተወያይተናልም ነው ያሉት፡፡

ኢትዮጵያ የCOP32 ፕሬዝዳንትነትን ለመረከብ በምታደርገው ዝግጅት ላይ የሚኖረውን አጋርነት እንዲሁም የጋራ ትኩረት በሚሹ ቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ለመተባበር የሚያስችሉ ዕድሎችን ተመልክተናል ሲሉም ገልጸዋል።

በሌላ በኩል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በCOP31 የመሪዎች ጉባኤ ጎን ለጎን ከባርቤዶስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ ሞትሊ ጋር የጋራ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ላይ ተወያይተናል ብለዋል።

‎በአቪዬሽን ትብብር እና የኢትዮጵያን የCOP32 ፕሬዝዳንትነት ለመደገፍ በሚደረገው አጋርነት ላይ መምከራቸውን የገለጹት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጋራ ፍላጎቶችን መሠረት በማድረግ የሁለትዮሽ ግንኙነታችንን ይበልጥ ለማስፋት እና ቅድሚያ የሚሰጣቸውን የወል ጉዳዮች ወደ ተጨባጭ ውጤቶች ለመቀየር የሚያስችል ምክክር አድርገናልም ብለዋል።