EthiopiaNews

የብሔራዊ ስትራቴጂ ሚኒስቴር ኢትዮጵያ ከኮኘ30 ቤሌም እስከ ኮኘ 31 አንታሊያ ያስመዘገበቻቸውን የአየር ንብረት ለውጥ ምላሽ ውጤቶች በዓለም አቀፍ መድረክ ማቅረቧን አስታውቋል።

ሚነስቴሩ ይህን ያስታወቀው ባወጣው መግለጫ ላይ ነው።

በቱርክ አንታሊያ እየተካሄደ በሚገኘው 31ኛው የተመድ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያ ባለፈው 1 ዓመት ውስጥ ዝቅተኛ የካርቦን ልቀትና የአየር ንብረት ተቋቋሚነት ያለው ኢኮኖሚ በመገንባት ረገድ ያስመዘገበቻቸውን ተጨባጭ ውጤቶችና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች ይፋ አድርጋለች ተብሏል።

በኮፕ 31 የኢትዮጵያ ፓቪሊዮን በብሔራዊ ስትራቴጂ ሚኒስቴር አዘጋጅነት “ከቤሌም እስከ አንታሊያ፦ ዝቅተኛ የካርቦን ልቀትና የአየር ንብረት ተቋቋሚ ኢኮኖሚ በመገንባት የኢትዮጵያ ጉዞ” በሚል መሪ ቃል በተካሄደው ከፍተኛ የግምገማ መድረክ፣ የኢትዮጵያ መንግሥትና የልማት አጋሮች ተወካዮች ተገኝተዋል።

በመድረኩ በሀገሪቱ ውስጥ የሚገኙ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ቁጥር 144,429 መድረሱ ተገልጿል።

ኢትዮጵያ የካርቦን ገበያ አዋጅ ማጽደቋ፣ የብሔራዊ የካርቦን መዝገብ ሥርዓት ማዘጋጀቷ ፣ እንዲሁም የአየር ንብረት መረጃ ማዕከልና የተቀናጀ የክትትል፣ ሪፖርትና ማረጋገጫ ሥርዓት መዘርጋቷን ገልጻለች።