InternationalNews

ኢራን በባህሬን የሚገኝን የአሜሪካ የአየር መከላከያ ራዳርን አጠቃሁ አለች።

የኢራን አብዮታዊ ዘብን ጠቅሶ ቲ አርቲ እንደዘገበው አብዮታዊ ዘቡ የአየር መቃወሚያ ራዳሩን ያጠቃው በሰው አልባ አውሮፕላኖች ሲሆን ዋሽንግተንንም ከተመሳሳይ ጥቃት እንድትታቀብ አሳስቧል።

አብዮታዊ ዘቡ ወሳኝና አውዳሚ ባለው በዚህ ጥቃት ስድስት ድሮኖችን መጠቀሙንና በዚህም በአል ራፋ የተተከለው የቅኝት ራዳር ከጥቅም ውጭ መሆኑን አመልክቷል።

አብዮታዊ ዘቡ አክሎም አሜሪካ የላከቻቸው በርካታ ድሮኖች ተመተው ወድቀዋል ብሏል።

አብዮታዊ ዘቡ ጦርነቱ እንደተጀመረ የተዘጋው የሆርሙዝ ሰርጥ አሁንም ዝግ መሆኑን አመልክቶ ይህ የሆነው የአሜሪካ ወታደሮች በሰርጡ የሚያልፉ መርከቦችን እናጅባለን በሚሉበት ወቅት ነው።