ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በመዲናዋ 57 ሄክታር የሚሸፍን አዲስ የኮሪደር ልማት ሥራን አስመረቁ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የቦሌ መድኅኒዓለም – 22 – ጎላጎል – እንግሊዝ ኤምባሲ መንገድና አካባቢን ገጽታ ሙሉ በሙሉ የቀየረውን የኮሪደር ፕሮጀክት በይፋ መርቀዋል።
ጠ/ሚ ዐቢይ የተሰራውን የኮሪደር ስራ ” ከመሠረተ ልማት ግንባታ በላይ ነው ” ያሉ ሲሆን ” ለአዲስ አበባ እና ለኢትዮጵያ ከተሞች መጻኢ ዕድል የተነደፈ ሰፊ ራዕይ አካል ነው ፤ ይኸውም ምርታማትን፣ አካታችነት፣ አረንጓዴነትንና የማይበገር ልማትን ያካተተ ነው ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ክንውኑም በሕዝቦቻችን ፍላጎት እና በመጪው ትውልድ መሻት ዙሪያ የተቃኘ ነው ሲሉ ገልጸዋል።
የአዲስ አበባ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በአጠቃላይ በግንባታ ወቅት 23,000 ዜጎች የሥራ ዕድል ማግኘታቸውን ገልጸው በቀጣይ ለ10 ሺ ሰዎች ቋሚ የሥራ ዕድሎች እንደሚፈጠሩ ተናግረዋል።
ከንቲባዋ መላው ህዝብ ይህንን የልማት ሥራ፣ ይህንን ውበትና አሻራ እንዲሁም ሀብትና ንብረት በባለቤትነት ስሜት ተንከባክቦ በመጠበቅ ለቀጣዩ ትውልድ እንዲተላለፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።
ከንቲባዋ ዘመናዊ እና ግዙፍ ሲሉ በጠሩት በዚህ የኮሪደር ልማት የተለያዩ የቦሌ አካባቢዎች የለሙ መሆኑን በዝርዝር አሳውቀዋል።
👉• ከቦሌ መድኃኒዓለም – ጎላጉል – እስከ እንግሊዝ ኢምባሲ
• ከቦሌ መድኃኒዓለም – እስከ ሞኤንኮ
• ከቦሌ ትምህርት ቤት – እስከ አደይ አበባ ሞዴል መንደር
• ከኢምፔሪያል ሆቴል – እስከ ሻላ መናፈሻ
• ከቺቺኒያ – እስከ ቦሌ ሩዋንዳ
• ከአደይ አበባ ስታዲየም – እስከ ቦሌ መንገድ
• የውስጥ ለውስጥ የመንገድ ኔትወርክ
👉አጠቃላይ የልማት ስፋትና መሠረተ ልማት ሰራዎች ፦
• 57 ሄክታር የልማት ቦታ
• 17 ኪ.ሜ. የመንገድ ርዝመት
• 34.ኪ.ሜ. የእግረኛ መንገድ
• 8 ኪ.ሜ. የሳይክል መንገድ
• 3 የተሽከርካሪና የእግረኛ መሻገሪያ ድልድዮች
• 5,880 መኪናዎችን በአንድ ጊዜ ማቆም የሚችሉ የመኪና ማቆሚያዎች
• 150 የኤሌክትሪክ መኪና ቻርጀሮች
• 13 የታክሲና አውቶቡስ መጫኛና ማውረጃ ቦታዎች
👉የመሬት ውስጥ መሠረተ ልማት ሰራዎች ፦
• 17 ኪ.ሜ. የፍሳሽና የጎርፍ ማስወገጃ መስመሮች
• 17 ኪ.ሜ. የመጠጥ ውሃ መስመሮች
• 17 ኪ.ሜ. የኤሌክትሪክ መስመሮች
• 17 ኪ.ሜ. የቴሌኮም መስመሮች
• 17 ኪ.ሜ. የITS መስመሮች
👉የንግድ፣ የሥራ፣ የመኖሪያና የመዝናኛ ልማት ሰራዎች ፦
• 91 የንግድ ሕንፃዎች
• 3,116 የንግድ ሱቆች
• 152 ቤቶችን የያዘ ሞዴል መንደር
• 33 ካፍቴሪያዎች
• 20 ሬስቶራንቶች
• 440 የታደሱ ሕንፃዎች
• 2 ቤተመጻሕፍት
• 7 የልጆች መጫወቻዎች
• 7 የስፖርት ሜዳዎችና ጂምናዚየሞች
• 7 ፏፏቴዎችና ፋውንቴኖች
• 5 የህዝብ መዝናኛና ፕላዛዎች
• ሰፊ አረንጓዴ ቦታዎች
• የህዝብ መፀዳጃ ቤቶች
👉የተቋማት ልማት ስራዎች ፦
• 2 የትምህርት ቤት ግንባታና ማስፋፊያ ሕንፃዎች
• 2 የፖሊስ ጣቢያ ግንባታና ማስፋፊያ ሕንፃዎች
• 1 የቱሪስት መረጃ ማእከል
