EthiopiaNews

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአፍሪካ 2ኛው ግዙፍ የደንበኞች መሠረት ያለው ባንክ መሆኑን አስታወቀ።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በ50.2 ሚሊዮን ደንበኞች 60 ሚሊዮን ደንበኞች ካሉት የናይጀሪያው አክሰስ ባንክ በመቀጠል በአፍሪካ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

ከስምንት አሥርተ ዓመታት በላይ ኢትዮጵያ የምጣኔ ሀብት ዋልታ ሆኖ መቆየቱን የገለፀው ባንኩ ከከተማ እስከ ገጠር በዘረጋው ሰፊ የአገልግሎት አድማስ እና በየጊዜው ተግባራዊ በሚያደርጋቸው በቴክኖሎጂ የተደገፉ አሠራሮች በደንበኞች ዘንድ ተመራጭ ሊሆን መቻሉን ገልጿል።

ባንኩ ከ3 ነጥበ 1 ትሪሊዮን ብር በላይ ሀብት እንዳለውና ይህም ከምሥራቅ አፍሪካ ቀዳሚው ባንክ እንደሚያደርገው ከ10 ቀናት በፊት ባወጣው መግለጫ መግለፁ ይታወሳል።