EthiopiaInternationalNews

አውስትራሊያ በመጪው አመት በአዲስ አበባ የሚካሄደው ኮፕ 32 የተሳካ እንዲሆን ለኢትዮጵያ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኗ ተገልጿል።

ይህ የተገለጸው የኮፕ 32 ዝግጅትን በተመለከተ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የኮፕ 32 ተመራጭ ፕሬዚዳንት ጌዲዎን ጢሞቲዎስ ከኮፕ 31 የድርድር ፕሬዚዳንት ክሪስ ቦወን ጋር የሁለትዮሽ ውይይት ባካሄዱበት ወቅት ነው።

የኮፕ32 ተመራጭ ፕሬዚዳንቱ ጌዲዎን ጢሞቲዎስ የኮፕ 31 ፕሬዚዳንትነት በድርድሩ ያሳየውን አመራር በማድነቅ ግልጽና አካታች ሂደቱን እንዲሁም እስካሁን የተመዘገበውን ውጤት አድንቀዋል።

የኮፕ 31 የድርድር ፕሬዚዳንት ክሪስ ቦወን በበኩላቸው ኢትዮጵያ ለኤሌክትሪፊኬሽን ትግበራ አጀንዳ ለሰጠችው ድጋፍ አመስግነው፣ ወደ ተጨባጭ ውጤቶች ለመቀየር ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል።