በትምህርት ሚኒስቴርና በክልል ትምህርት ቢሮዎች ትብብር በመላ አገሪቱ እየተገነቡ ያሉ ከ1 ሺህ 400 በላይ ሞዴል የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በመጠናቀቅ ላይ መሆናቸው ተገልጿል።
እነዚህ ትምህርት ቤቶች ቀደም ሲል ምንም ዓይነት የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ባልነበሩባቸው አካባቢዎች ላይ ትኩረት ተደርገው የተገነቡ እንደሆነ ነው የተነገረው።
ግንባታው ትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ጥራትን ከመሠረቱ ለማረጋገጥ ከጀመራቸው የሪፎርም ሥራዎች መካከል አንዱ መሆኑም ተጠቁሟል።
