የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ማሻሻያ የአሜሪካ ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ፍላጎት እንዲጨምር እያደረገ መሆኑ ተገለጸ።
ይህ የተባለው የገንዘብ ሚኒስትር ፍጹም አሰፋ፣ የብሔራዊ ባንክ ገዥ እዮብ ተካልኝና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሃደራ አበራ ከአሜሪካ የውጭ ግንኙነት ካውንስል ልዑካን ቡድን አባላት ጋር በተወያዩበት ወቅት ነው፡፡
የአሜሪካ አልሚዎች በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ለመግባት የኢንቨስትመንት ዕድሎችን እየተመለከቱ እንደሆነም በዚሁ ወቅት ተጠቁሟል።
እንዲሁም ውይይቱ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ማሻሻያ፣ የኢንቨስትመንት አማራጮች፣ በቀጣናዊ የፖለቲካና የኢኮኖሚ መስኮች ላይ ትኩረት ያደረገ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን የአሜሪካ የውጭ ግንኙነት ካውንስል ፕሬዚዳንትና የልዑካኑ መሪ ማይክል ፍሮማን በበኩላቸው የኢትዮጵያ አጠቃላይ የኢኮኖሚ ሥርዓት አስደናቂ ዕድገት እያስመዘገበ ነው ብለዋል።
