EthiopiaNews

በመቐለ ከተማ ባለፉት 30 ቀናት ሰላምን በማስፈን፣ መንግሥታዊ ተቋማትን እና የንግድ እንቅስቃሴዎችን ወደ መደበኛ ሥራ በመመለስ ረገድ ውጤታማ ተግባራት መከናወናቸውን በክልሉ ባለአደራ አስተዳደር፤ የከተማዋ ከንቲባ ሽሻይ አማረ አስታወቁ።

መንግሥታዊ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት ሥራ በመጀመራቸው ሠራተኞች ወደ ሥራ ገበታቸው ተመልሰው የደመወዝ ክፍያ እንዲፈጸምላቸው ተደርጓል ያሉት ከንቲባው ሆኖም ሠራተኞች የሥራ ሰዓትን አክብሮ በመግባት ረገድ ውስን ክፍተቶች መኖራቸው በግምገማ ላይ መነሳቱንም ጠቅሰዋል፡፡

በንግዱ ዘርፍም በተቀመጠው አቅጣጫ መሠረት እንቅስቃሴዎች ወደ መደበኛ ሁኔታ መመለሳቸው፣ እንዲሁም መሠረታዊ ሸቀጦች እና ነዳጅ ወደ ከተማዋ መግባት መጀመራቸው የተሻለ የኢኮኖሚ መነቃቃት እንዲፈጠር አስተዋጽኦ አድርጓል ነው የተባለው።

ከዚህ ባለፈ የመንገድ እና ትራንስፖርት ቢሮ የከተማዋን አውቶቡስ ተርሚናል በመክፈት፣ ወደ መቐለ የሚገቡ እና የሚወጡ ጉዞዎች ሰላማዊ እና ደኅንነታቸው የተጠበቀ እንዲሆን ከፍተኛ ሥራ ማከናወኑ ተገልጿል።