የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ 26ኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 10 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር እሁድ ህዳር 13 2019 ዓ.ም እንደሚካሄድ ተናገሩ።
ሚኒስትሯ ይሄን ያሉት ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው።
ሚኒስትሯ ሰላማዊት ካሳ ታላቁ ሩጫ ከጎዳና ሩጫ ባሻገር ዘርፈ ብዙ ፋይዳ ያለው ወሳኝ ስፖርታዊ ኩነት ነው ብለዋል።
በዓለም አትሌቲክስ ዕውቅና የተሰጠው ይህ ታላቅ ውድድር፣ እስካሁን የአፍሪካ ትልቁ የጎዳና ላይ ሩጫ ሆኖ መቆየቱን ያነሱት ሚኒስትሯ አሁን ደግሞ በዓለም አቀፍ ደረጃ ትልቁ የ10 ኪሎ ሜትር ውድድር እንዲሆን ለተጀመረው ጥረት የዘንድሮው ውድድር ትልቅ አቅም የሚፈጥር መሆኑን አስገንዝበዋል።
በዓለም አቀፍ ደረጃ የኢትዮጵያን የአትሌቲክስ ልዕልና፣ የእንግዳ ተቀባይነት ባህል እና የመዲናዋን ዘመናዊ የከተማ ገጽታ ለዓለም የሚያስተዋውቀው 26ኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በመጪው እሁድ በደማቅ ሁኔታ ይካሄዳል።
በውድድሩ ታሪክ 60 ሺህ ተሳታፊዎች በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ ይሮጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።
