የጤና ሚኒስቴር በሃገር አቀፍ ደረጃ እስከ ነገ በሚቀጥለው የፖሊዮ የክትባት ዘመቻ 11 ነጥብ 3 ሚሊዮን ህፃናት እንደሚከተቡ አስታወቀ።
ሚኒስቴሩ ይሄን ያለው ሀገር አቀፍ የተቀናጀ የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ ማስጀመሪያ መርሃ ግብር በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጨንቻ ከተማ መካሄዱን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ ነው።
በማስጀመሪያ ፕሮግራሙ ላይ ከጤና ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት፣ ደቡብ ክልል ጤና ቢሮ፣ ጋሞ ዞን፣ የአለም ጤና ድርጅት እና ሌሎች አጋር ድርጅቶች ተገኝተዋል።
የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ተወካይ መስፍን ወሰን ዘላቂ የሆነ የአካል ጉዳትን ብሎም ሞትን የሚያስከትለው የፖሊዮ በሽታን ለማጥፋት እንደ አለም የሚደረገው ርብርብ አካል የሆነው ይህ የክትባት ዘመቻ ከህዳር 12 እስከ 15 2019 ዓ.ም የሚካሄድ እና 11.3 ሚሊዮን ህፃናት የሚከተቡበት መሆኑን ገልፀዋል።
በዘመቻው ከፖሊዮ ክትባት ጎን ለጎን ሌሎች የጤና መረጃዎችን የማሰባሰብ የተቀናጁ ተግባራት እንደሚከናወኑ ተናግረዋል።
ክትባቱ በቤት ለቤት እና በተለያዩ ተቋማት የሚሠጥ መሆኑን በመግለጽ በየእርከኑ የሚገኙ የመንግስት አካላት፣ የኃይማኖት ተቋማት እና የሚዲያ አካላት ለዘመቻው ስኬታማነት እንዲተባበሩ አቶ መስፍን ጥሪ አስተላልፈዋል።
የአለም የጤና ድርጅት የፖሊዮ ክትባቱ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፣ በኦሮሚያ፣ በማእከላዊ ኢትዮጵያ ፣ በደቡብ ኢትዮጵያ እና በደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ክልሎች እየተሰጠ መሆኑን ገልጿል።
የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ናፍቆት ብርሃኑ ፖሊዮ ዘላቂ ለዘመቻው ስኬት ሁሉም ሚናውን እንዲወጣ አሳስበዋል።
