EthiopiaNews

የኢትዮጵያ አየርመንገድ የካርጎ እና ሎጂስቲክስ አገልግሎት በፈረንጆቹ 2026 አመት በተካሄደው የአረቢያን ካርጎ ሽልማት ላይ ለተከታታይ 4ኛ ጊዜ የአፍሪካ ምርጥ የካርጎ አየር መንገድ በመባል አሸነፈ።

አየር መንገዱ ይሄን ያለው ባወጣው አጭር መግለጫ ነው።

ይህ እውቅና የኢትዮጵያ ካርጎ እና ሎጂስቲክስ አገልግሎት በአፍሪካና በመላው ዓለም ፈጣን፣ ቀልጣፋና ጥራቱን የጠበቀ የካርጎ ማጓጓዝ አገልግሎት በላቀ ሁኔታ እየሰጠ መሆኑን የሚያሳይ ነው ተብሏል።

በሌላ በኩል የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሚሰጣቸው የተለያዩ አገልግሎቶች ላሳየው የላቀ ብቃት ለ13ኛ ዙር በተዘጋጀው የኢትዮዽያ ሀገር አቀፍ የጥራት ውድድር ላይ ከኢትዮጵያ የጥራት ቁጥጥር ተቋም የእውቅና ሽልማት ማግኘቱን ገልጿል።