EthiopiaNews

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የኮፕ 32 ተመራጭ ፕሬዝዳንት ጌዲዎን ጢሞቲዎስ የኢትዮጵያን ራዕይ በማቅረብ የኮፕ 32 ቅድሚያዎችን ይፋ አደረጉ።

ጌዲዎን ጢሞቲዎስ በኮኘ 31 ጉባኤ የመዝጊያ ሥነ ሥርዓት ላይ ባደረጉት ንግግር የኮፕ 32 ቅድሚያዎቻችን ተስፋን መመለስ፣ መተማመንን እንደገና መገንባት እና የጋራ እርምጃን ማነቃቃት ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያ አካታችና ግልጽ ሂደት በመከተል፣ የሁሉንም ወገኖች ድምፅ በማዳመጥና በጋራ በመስራት ስምምነትን ለመገንባት እንዲሁም ትርጉም ያለው ውጤት ለማስመዝገብ ትሰራለች ብለዋል።

በአንታልያ የተፈጠረውን መነቃቃት በመቀጠል፣ አዲስ አበባ ቀጣዩን ጉባኤ ለመምራት እየተዘጋጀች መሆኑን ነው የኮፕ 32 ተመራጭ ፕሬዝዳንቱ የጠቀሱት።

በቱርክ አንታሊያ ሲካሄድ የቆየው 31ኛው የተመድ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ የተጠናቀቀ ሲሆን ኢትዮጵያ በሚቀጥለው ዓመት 32ኛውን የተባበሩት መንግሥታት የአየር ንብረት ጉባኤ ኮፕ 32 በአዲስ አበባ ለማስተናገድ ያላትን ዝግጁነት በድጋሚ በመዝጊያ ስነ ስርዓቱ ላይ አረጋግጣለች።