ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የፊታችን ሐሙስ ህዳር 17 ቀን 2019 አ.ም በሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ቀርበው ማብራሪያ እንደሚሰጡ ም/ቤቱ አስታወቀ።
ም/ቤቱ ይሄን ያለው ዛሬ ባወጣው መግለጫ ነው።
7ኛው የህዝብ እንደራሴዎች ም/ቤት 1ኛ አመት የስራ ዘመን 4ኛ መደበኛ ጉባኤ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በሚገኙበት ህዳር 17 ቀን 2019 ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ እንደሚካሄድ ነው ም/ቤቱ ያስታወቀው።
ም/ቤቱ ርዕሰ ብሔር ታዬ አፅቀስላሴ ያለፈው መስከረም 26 2019 አ.ም በጋራ መክፈቻ ጉባዔው ላይ ያቀረቡትን የ2019 አመት የመንግስት እቅድ መነሻ በማድረግ ከም/ቤት አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች እና አስተያየቶች ጠቅላይ ሚኒስትሩ ማብራሪያ ይሰጣሉ ብሏል።
ይህን ተከትሎ ም/ቤቱ የመንግስትን አቋም በማዳመጥ ሞሽኑን ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።
በእለቱ በአዲስ አበባ የሚገኙ የተለያዩ ሃገራት አምባሳደሮች ፣ የአለም ተቋማት ተጠሪዎች እና ሌሎችም እንግዶች በእንግድነት እንደሚታደሙ ተገልጿል።
ጉባዔው በተለያዩ የሚዲያ አማራጮ ች በቀጥታ ስርጭት እንደሚተላለፍ ም/ቤቱ አስታውቋል።
