EthiopiaNews

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የንግድ ህጉን በተላለፉ 61 የዳቦ አምራቾች ላይ አስተዳደራዊና ህጋዊ እርምጃ መውሰዱን አስታወቀ።

ቢሮው ይሄን ያለው ባወጣው መግለጫ ነው።

ቢሮው በመዲናዋ ከሚገኙ ዳቦ ቤቶች 188ዱ ላይ ምልከታ ያደረገ ሲሆን ዋጋ ዝርዝር ያለመለጠፍ፣ 70 ግራም ዳቦ ከ13 ብር በላይ የመሸጥ፣ ከ70 ግራም በታች የሆነ ዳቦ ለሽያጭ ማቅረብ እና ሌሎች የህግ ጥሰቶች ተፈፅመው በመገኘታቸው በ61ዱ ላይ የመጀመሪያ ደረጃ ህጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ መወሰዱን ገልጿል።

የቢሮው የሬጉላቶሪ ዘርፍ ምክትል ቢሮ ኃላፊ ፀጋዬ ደበሌ በመዲናዋ የተረጋጋ የግብይት ስርዓት ከመፍጠር አንፃር የንግድ ህጉን መሠረት በማድረግ ጠንከር ያለ የቁጥጥር ስራ እየተሠራ መሆኑን ገልዋል።

አቶ ፀጋዬ አያይዘውም ከዳቦ ግብይት አንፃር አምራቾች በስቀመጡት ስታንዳርድና ዋጋ መሠረት የመሸጥ ሃላፊነት እንዳለባቸው ገልፀው እየተወሰደ ያለው እርምጃ በቀጣይ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

ሸማቹ ማህበረሰብ በግብይት ሂደት የሚፈፀሙ ህገ-ወጥ ተግባራትን አይቶ ከማለፍ ይልቅ በ85 88 በመደወል አሊያም አቅራቢያው ለሚገኙ የንግድ ፅ/ቤት ቁጥጥር ባለሙያዎች በማሳወቅ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ መልዕክት አስተላልፈዋል።

መረጃው ከአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የተገኘ ነው።