InternationalNews

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሩሲያው አቻቸው ቭላድሚር ፑቲን በመላው አውሮፓ የሚፈጽሙትን ወታደራዊ  እንቅሰቃሴእንዲያቆሙ መጠየቃቸውን አስታወቁ።

ፕሬዝዳንት ትራምፕ ባለፈው ሳምንት በቻይና ሼንዘን ከተማ ከፕሬዝዳንት ፑቲን ጋር ባደረጉት ውይይት የዩክሬንን ጦርነት በፍጥነት በስምምነት ለመቋጨት ሲባል ሩሲያ በአውሮፓ ግዛቶች ላይ የምታደርገውን ወታደራዊ ጫና እንድትቀንስ  ለፑቲን መንገራቸውን ገልጸዋል።

ትራምፕ ፑቲን የሰላም ስምምነት ማድረግ እንደሚፈልጉ ቢያምኑም በሩሲያው መሪ እና በዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎዲሚር ዘሌንስኪ መካከል ያለው ከፍተኛ ጥላቻ ድርድሩን አስቸጋሪ እንዳደረገው ተናግረዋል።

በተጨማሪም ትራምፕ በመጪው የፈረንጆቹ ታህሳስ ወር በፍሎሪዳ በሚካሄደው የቡድን 20 ሀገራት ጉባኤ ላይ ፑቲን እንዲሳተፉ ፍላጎት እንዳላቸው ሲገልጹ፣ ክሬምሊን በበኩሉ ስለ ተሳትፎው እስካሁን የተወሰነ ነገር አለመኖሩን አስታውቋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ፖላንድ የሩሲያ ጦር አውሮፕላኖች የአየር ክልሏን ሆን ብለው ጥሰዋል ስትል ስትከስ፣ የትራምፕ የዲፕሎማሲ መልዕክተኛ ጃሬድ ኩሽነር ግን ፑቲን የኒውክሌር መሳሪያ ባለመጠቀም ታላቅ የፖለቲካ ብስለት አሳይተዋል ሲሉ ማድነቃቸው ተመልክቷል።