የአዲስ አበባ ከተማ የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ 9ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ ውጤት ህዳር 24 ቀን 2019 ዓ.ም በኦንላይን ይፋ እንደሚደረግ አስታውቋል።
ቢሮው ይሄን ያለው ባወጣው መግለጫ ነው።
የጨረታ ኮሚቴ አስተባባሪው አቶ ክብሮም አሰፋ 9ኛ ዙር የመሬት ሊዝ ጨረታ ጊዚያዊ ውጤት መጪው ሐሙስ ህዳር 24 ቀን 2019 ዓ.ም በበይነ-መረብ ለህዝብ ይፋ እንደሚደረግ ተናግረዋል።
አቶ ክብሮም ይህንን የገለጹት ዛሬ ለም ሆቴል አካባቢ በሚገኘው የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ፣ ተጫራቾች የጨረታ ሲፒኦ ባስረከቡበት ወቅት ነው።
እንደ አስተባባሪው ገለጻ የጨረታ ሂደቱን ግልጽነትና ቀልጣፋነት ለማረጋገጥ ሲባል ውጤቱን በኦንላይን ይፋ ለማድረግ ዝግጅት መደረጉን ጠቁመው ፤ ተጫራቾች በተጠቀሰው ቀን ቢሮ መምጣት ሳያስፈልጋቸው ባሉበት ሆነው በበይነመረብ አማካኝነት ውጤታቸውን መከታተል እንደሚችሉ ገልጸዋል።
ተወዳዳሪዎች በጨረታው ያላቸውን ቅሬታ ከህዳር 24/2019 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ አምስት የስራ ቀናት የጨረታ ሰነድ በገዙበት ድረገጽ https://addislandfarm.gov.et
ማቅረብ እንደሚችሉም አስተባባሪው ጨምረው ገልጸዋል።
