EthiopiaNews

መቀመጫውን በአረብ ኢምሬትስ ያደረገው የሞሐመድ ቢን ዛይድ ፋውንዴሽን ፎር ሂዩማኒቲ ኢትዮጵያን ጨምሮ ለ9 የአፍሪካ ሃገራት የጤና ተቋማትን ለመደገፍ የሚውል 135 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ይፋ አደረገ።

ፋውንዴሽኑ ይሄን ድጋፍ ይፋ ያደረገው በአዲስ አበባ በተካሄደው እና ዛሬ በተጠናቀቀው የአፍሪካ የሕብረተሰብ የጤና ጉባኤ ጎን ለጎን በተካሄደ ስብሰባ ላይ ነው።

ድጋፉ ኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ላይቤሪያ፣ ማላዊ ፣ ናይጄሪያ፣ ሩዋንዳ ፣ጋና፣ ሴራሊዮን እና ሞዛምቢክን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ የተገለጸ ሲሆን ለጤና ተቋሟት የመድሃኒት ድጋፍ እና ህክምና ግብአቶችን ለማቅረብ ይውላል ተብሏል።