ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የአካባቢ ምርጫ ከአንድ አመት በኋላ ሊካሄድ እንደሚችል ገለጹ፡፡
በትላንትናው ዕለት የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ባካሄደው አራተኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ የአካባቢ ምርጫና የሕዝብ ቆጠራን በተመለከተ ጥያቄ የቀረበላቸው ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰጡት ምላሽ ከአንድ ዓመት በኋላ የአካባቢ ምርጫ ሊካሄድ እንደሚችል ጠቁመዋል፡፡
በየ10 አመቱ መካሄድ ያለበትና ላለፉት አመታት ያልተካሄደው የህዝብና ቤቶች ቆጠራን በተመለከተ በሰጡት ምላሽ ደግሞ ከዚህ በፊት ቆጠራውን ማድረግ የማያስችሉበት ሁኔታዎች እንደነበሩ በማንሳት በቀጣይ ነገሮች መልክ ሲይዙ የምናካሂድ ይሆናል ነው ያሉት፡፡
