የአለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ሂዩማን ራይትስ ዎች የትግራይ ባለስልጣናት እድሜያቸው 15 አመት የሆኑ ታዳጊዎችን ጨምሮ ሲቪል ሰዎችን በግዳጅ ለውትድርና እየመለመሉ መሆኑን አስታወቀ።
የአለም አቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋች ሂዩማን ራይትስ ዎች የትግራይ ባለስልጣናት እድሜያቸው 15 አመት የሆኑ ታዳጊዎችን ጨምሮ ሲቪል ሰዎችን በግዳጅ ለውትድርና እየመለመሉ መሆኑን አስታወቀ።
ሂዩማን ራይትስ ዎች ይሄን ያለው የትግራይ ባለስልጣናት እያደረጉ ያሉትን አስገዳጅ ወታደራዊ ምልመላ እንዲያቆሙ በጠየቀበት መግለጫ ነው።
የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ የትግራይ ባለስልጣናት ቤት ለቤት በሚደረግ አሰሳ ፣ በመስሪያ ቤቶች ፣ ከወርቅ ማእድን ማውጫዎች ሁሉ ታዳጊዎችን ጨምሮ የተለያዩ ሲቪል ዜጎችን ለወታደራዊ ግዳጅ እየመለመሉ መሆኑን አስታውቋል።
የድርጅቱ የአፍሪካ ክፍል ምክትል ኃላፊ ላቴሺያ ባድር በትግራይ የሚደረገው ይሄው ወታደራዊ ምልመላ ዜጐችን ለከፍተኛ ፍርሃት መዳረጉን ተናግረዋል።
ኃላፊዋ ላቴሺያ ባድር የክልሉ ባለስልጣናት እያካሄዱት ያለውን ወታደራዊ ምልመላ በአስቸኳይ እንዲያቆሙ እና በግዳጅ አፈሳው የተያዙ ሰዎችን እንዲለቁ ጠይቀዋል።
ተሟጋቹ በትግራይ ክልል ወታደራዊ ምልመላ እየተደረገ መሆኑን የሚያሳዩ 6 ማስረጃዎች መዝግቦ መያዙን ገልጿል። መረጃው ከሂዩማን ራይትስ ዎች የተገኘ ነው።
#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
