EthiopiaNews

ኮሚሽን ይሄን ያስታወቀው የ2018 በጀት አመት እቅድ አፈፃፀምን በገመገመበት መድረክ ነው።

ኮሚሽኑ በተጠናቀቀው በጀት አመት 4.32 ቢሊዮን ዶላር የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ወደ ሀገር መሳብ መቻሉን ገልፆ ይህም ከአምና ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀርም የ8 በመቶ ብልጫ እንዳለው ገልጿል።

ኢትዮጵያ በ2018 በጀት አመት የሳበችው የውጭ ኢንቨስትመንት ዘንድሮ በተደረገው የኢንቨስት ኢትዮጵያ ፎረም ላይ ቃል የተገቡ እና በቅርቡ ከኮሚሽኑ የኢንቨስትመንት ፈቃድ የወሰዱት ድርጅቶችን የማይጨምር መሆኑ ተገልጿል::

ኮሚሽኑ በበጀት አመቱ ከልዩ ኢኮኖሚ ዞኖች የ225 ሚሊዮን ዶላር ምርት ለውጭ ገበያ ማቅረብ የተቻለ መሆኑን ገልፆ ይህም የኮሚሽኑን የዕቅድ ግብ 100 በመቶ ያሳካ እና ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ80 በመቶ ጭማሪ ያሳየ መሆኑን አስታውቋል።

ኮሚሽኑ በበጀት ዓመቱ 528 አዳዲስ የኢንቨስትመንት ፈቃዶችን መስጠት መቻሉን ገልጿል።

በበጀት አመቱ ከ260 በላይ ፕሮጀክቶች ወደ ትግበራ መግባታቸው በኮሚሽኑ መግለጫ ተጠቅሷል።መረጃው ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የተገኘ ነው።