InternationalNews

የተባበሩት መንግስታት የስደተኞች ኤጀንሲ ሟቾቹ በጦርነት እየታመሰች ከምትገኘው ማይናማር ወደ ሌሎች አጎራባች ሀገራት ለመድረስ በመሰደድ ላይ የነበሩ መሆናቸውን ጠቁሟል፡፡

ስደተኞቹ ባለፈው ወር በሁለት የእንጨት ጀልባዎች ጉዞ የጀመሩ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ ከፊሎቹ ከማይናማር ቀሪዎቹ ደግሞ ከባንግላዴሽ የማይናማር ስደተኞች መጠለያ ተነስተው ወደ ማሌዢያ፣ ታይላንድና ኢንዶኔዢያ ለመድረስ መሞከራቸው ተነግሯል፡፡

የመጀመሪያው ጀልባ 250 ስደተኞችን ጭኖ ጉዞ እንደጀመረ ደብዛው መጥፋቱ ሲነገር ሁለተኛው ጀልባ ደግሞ 280 ስደተኞችን ጭኖ ጉዞ ከጀመረ በኋላ ከሳምንት በፊት በዚያው በማይናማር የባህር ዳርቻ አቅራቢያ ሳይሰምጥ አልቀረም ተብሏል፡፡