የተመድ የህፃናት መርጃ ዩኒሴፍ ክትባት ካላገኙት 13 ነጥብ 5 ሚሊየን ህፃናት ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት እንደሚገኙ ገልጿል።
ክትባት ያላገኙ ህጻናት በብዛት ከሚገኙባቸው 10 የአፍሪካ ሃገራት ውስጥ ኢትዮጵያ መካተቷን ዘ ኢንዲፔንደንት ዘግቧል።
ክትባት አላገኙም ተብለው ከተለዩት አጠቃላይ ህጻናት ውስጥ ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ግጭት ባሉባቸው ሃገራት ያሉ ናቸው ተብሏል።
ዩኒሴፍ በእነዚሁ ሃገራት የሚካሄዱ የክትባት ስራዎች መዘግየት አሳሳቢ ነው ብሏል።
