የጤና ሚኒስቴር ይሄን ያስታወቀው በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ዙሪያ ትናንት ባካሄደው ሃገር አቀፍ የተቀናጀ የጤና አገልግሎት ዘመቻ የማስጀመሪያ መርሀ ግብር ላይ ነው።
ቴልኮም ፕላስ በሚል ስያሜ ከሐምሌ 13 እስከ 24/2018 ዓ.ም የሚካሄደው ይህ የተቀናጀ የጤና ዘመቻ በ8 ክልሎች በአማራ፣ በኦሮሚያ፣በቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ በጋምቤላ፣ በሲዳማ፣ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ በደቡብ ኢትዮጵያና በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልሎች እንደሚካሄድ ተገልጿል።
ሚነስቴሩ በ8ቱ ክልሎች ውስጥ በተመረጡ 401 ወረዳዎች ላይ የጤና አገልግሎት ዘመቻው እንደሚከናወን እና ከ41 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ተጠቃሚ እንደሚሆኑ አስታውቋል።
በዘመቻዉ ከፍተኛ ተፅዕኖ ያላቸው 7 የጤና አገልግሎቶችን ያቀናጀ የትራኮማ፣ የዝሆኔ በሽታ እና የፎከት የጅምላ መድኃኒት እደላ፣ የዓይን ጤና ምርመራ፣ የወባ፣ የቲቢ እና የማህፀን በር ጫፍ ካንሰር ምርመራዎችን የሚያካትት መሆኑ ተገልጿል።
በኢትዮጵያ የዓለም ጤና ድርጅትና የአጋር ድርጅቶች ተወካይ ዶ/ር ሳራይ ማሉሞ በበኩላቸው ይህ አይነት ዘመቻ ፍትሀዊ ተጠቃሚነትን ከማረጋገጥ ባለፈ ወጪን በመቀነስ በተቀናጀ መልኩ አገልግሎት ለመስጠት እንደሚረዳ ጠቅሰው በቀጣይም ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስታውቀዋል፡፡
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ መና መኩሪያ በክልሉ በ8 ዞኖች ባሉ 25 ወረዳዎች ዘመቻው እንደሚካሄድና ከ1.6 ሚሊዮን በላይ ዜጎች ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ገልጸዋል፡፡መረጃው ከጤና ሚኒስቴር የተገኘ ነው።
