EthiopiaNews

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አክሎም የግድቡ የአርማታ ሙሌት ግንባታ ከመከናወኑ በፊት ከ7 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ በላይ ልል አፈር የማንሳት ሥራ መሰራቱንም ገልጿል።

በአሁኑ ወቅት ከ7 ነጥብ 7 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ በላይ የአርማታ ሙሌት ውስጥ ከ6 ነጥብ 2 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ በላይ የአርማታ ጥቅጥቅ ሙሌት መጠናቀቁም ተጠቁሟል፡፡

የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ እና ከጊቤ 3 የኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች ቀጥሎ 3ኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ይህ ግዙፍ የሃይል ማመንጫ ግንባታውን ለማፋጠን በ2 ፈረቃ እየተሰራ መሆኑን የገለጸው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በየወሩ በአማካኝ ከ100 ሺህ ሜትር ኪዩብ በላይ የአርማታ ጥቅጥቅ ሙሌት እየተከናወነ እንደሚገኝም ገልጿል።