EthiopiaNews

ከተሰሩ ስራዎች መካከል የወንዝ ዳርቻ የማስፋፋት ሥራዎች፣ በወንዞች የተከማቸ ደለል የማውጣት ሥራዎች፣ የጎርፍ መከላከያ ግድብ ግንባታና ማጠናከሪያ ሥራዎች፣ የጎርፍ ስጋትን የሚቀንሱ የመከላከያ መሠረተ ልማቶችና ሌሎች የቴክኒክ ጣልቃ ገብነቶች ተጠቅሰዋል።

ይህ የተባለው በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የሚተገበረው የኢትዮጵያ ብሔራዊ የጎርፍ መከላከል ፕሮጀክት የ2018 ዓ.ም ዓመታዊ የአፈጻጸም ግምገማ መድረክ ሲሆን ፕሮጀክቱ በሃገሪቱ ጎርፍ በተደጋጋሚ የሚያጠቃቸውን አካባቢዎች የሚደቀንባቸውን የአደጋ ስጋት ለመቀነስና ከችግሩ ለማላቀቅ እንዲቻል በአዋሽ፣ በኦሞ ጊቤና ስምጥ ሸለቆ ሃይቆች ዙሪያ የተቀናጀ የውሃ ሀብት አስተዳደርን ለማስፈን ታልሞ መቋቋሙ ተገልጿል።

በአለም ባንክ የሚደገፈው ይህ ፕሮጀክት 635 ሺህ የማህበረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ለማድረግ አቅዶ የተለያዩ ስትራቴጂዎችን በመቀየስ በበጀት ዓመቱ ስራዎችን ሲተገብር መቆየቱም በመድረኩ ተገልጿል።

የጎርፍ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት ከኢንዱስትሪዎች፣ ከዩኒቨርሲቲዎችና ከተለያዩ የምርምር ተቋማት ጋር በትብብር የሚሰሩ የኢንዱስትሪ ዩኒቨርሲቲ ቁርኝት ፕሮግራሞችና ለዘላቂ የጎርፍ አስተዳደር የሚያገለግል የመመሪያ ሰነድ ዝግጅት ላይ የተከናወኑ ሥራዎች በሪፓርቱ ተጠቅሰዋል።