በክሪፕቶ ከረንሲዎች ላይ ብቻ ሳይሆን፣ ለክፍያና ለኢንቨስትመንት በሚውሉ የዲጂታል ወይም ኤሌክትሮኒክ ሀብቶች ላይ ጭምር ክልከላው ተፈጻሚ እንደሚሆንም ነው ባንኩ ባወጣው ማሳሰቢያ የገለጸው።
በበይነ መረብ ጥቃቶች እና በገበያ ማጭበርበር ምክንያት ሊደርሱ ከሚችሉ ከፍተኛ የፋይናንስ ኪሳራዎች ኅብረተሰቡ እንዲጠነቀቅ ያሳሰበው ባንኩ በተጨማሪም ምናባዊ ሀብቶችን የሚያካትቱ ማንኛውንም ግብይቶችና እንቅስቃሴዎች ላይ ከመሳተፍ እንዲቆጠቡም አስጠንቅቋል፡፡
