EthiopiaNews

ኢትዮጵያ የያዘችውን የዲጂታላይዜሽን ውጥን እውን ለማድረግ የኤሌክትሪክ ተደራሽነት ማስፋፋት ወሳኝ ነው ያሉት የአገልግሎቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ጌቱ ገረመው፤ በፍጥነት እያደገ የመጣውን የኃይል ፍላጎት ለማመጣጠን፣ የኔትወርክ ችግሮችን ለመፍታትና የኃይል ስርጭትን ወደ ዲጂታል አሠራር ለማሽጋገር የሚያስችል የ25 ዓመት የማሻሻያ ጥናት ይፋ ሆኗል ነው ያሉት፡፡

ፕሮጀክቱ የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተደራሽነትና ጥራት የሚያረጋግጥ ሲሆን፤ ኢንደስትሪዎች እንዲስፋፉና ለዜጎች የሥራ እድል በመፍጠር ለኢኮኖሚው ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዲሰጡ የሚያስችል መሆኑንም ነው ያስረዱት፡፡

ጥናቱ በዓለም ባንክ የገንዘብ ድጋፍና ሞኔንኮ ኢራን ኢንጅነሪንግ ኮንሰልቲንግ በተሰኘ የኢራን አማካሪ ድርጅት የተዘጋጀ ነው ተብሏል፡፡

ከዓለም ባንክ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ለተከናወነው ጥናት ከ4 ነጥብ 7 ሚሊየን ዩሮ በላይ ወጪ ስለመደረጉ ተነግሯል፡፡

ጥናቱን ሙሉ በሙሉ ለመተግበርም 30 ነጥብ 65 ቢሊየን ዶላር ብሔራዊ ኢንቨስትመንት እንደሚያስፈልግ ነው የተመለከተው፡፡

በ30 ነጥብ 65 ቢሊየን ዶላር የሚተገበር የሃይል ሥርጭት ማስተር ፕላን ፕሮጀክት ይፋ ማድረጉንም  የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት አስታውቋል፡፡