EthiopiaNews

ባለስልጣን መ/ቤቱ ይሄን ያለው የካፒታል ገበያ ግንዛቤን ለማስፋት ጥሩ ውጤት ላላቸው የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የመጨረሻ አመት ተማሪዎች እና የቅርብ ጊዜ ተመራቂዎች ያዘጋጀዉን ሁለተኛውን የሰመር ካምፕ መርሃ ግብር ባስጀመረበት መድረክ ላይ ነው።

ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ የሚያዘጋጀው ይህ መርሃ ግብር ከፍተኛ ውጤት ያላቸው የዩኒቨርሲቲ የመጨረሻ ዓመት ተማሪዎች እና የቅርብ አመት ተመራቂዎች ስለ ካፒታል ገበያው እና ሥነ-ምህዳሩ በቂ እውቀት እና ግንዛቤ ኑሯቸው በገበያው ተሳታፊ እንዲሆኑ ለማስቻል ያለመ ነው፡፡

መርሃ ግብሩን የኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሀና ተኸልቁ ያስጀመሩት ሲሆን ሰልጣኞች ስለ ካፒታል ገበያው በቂ ግንዛቤ የሚያገኙበት እንዲሁም በገበያው ላይ በተለያዩ ዘርፎች ተሳታፊ ሊሆኑ የሚችሉበትን እድል የሚፈጥር መሆኑን ገልፀዋል።

ሰልጣኞች በቆይታቸው ንቁ ተሳትፎ በማድረግ በካፒታል ገበያው ዙሪያ በቂ ግንዛቤ ማግኘት እንዲሁም በካፒታል ገበያው ተሳታፊ ለመሆን መዘጋጀት እንዳለባቸውም ዋና ዳይሬክተሯ አሳስበዋል፡፡

ይህ የሰመር ካምፕ የስልጠና መርሃ ግብር ለቀጣይ ሁለት ሳምንታት በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች የሚሰጥ ሲሆን ስልጠናው በቂ ግንዛቤ ያገኙ እና በገበያው ተሳታፊ ሊሆኑ የሚችሉ ወጣቶችን ለማፍራትም መልካም እድልን ይፈጥራል ተብሏል፡፡ መረጃው ከኢትዮጵያ የካፒታል ገበያ ባለሥልጣን የተገኘ ነው።