የኢትዮጵያ ባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ በተጠናቀቀው 2018 በጀት ዓመት ከ157 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ማግኘቱን ይፋ አደረገ።
የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አብዱልበር ሸምሱ (ኢ/ር) ይሄን ያስታወቁት ትናንት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው፡፡
ዋና ሥራ አስፈጻሚው በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት 144.9 ቢሊየን ብር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ 157.2 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን ተናግረዋል።
በበጀት ዓመቱ ከግብር በፊት 28.2 ቢሊየን ብር ትርፍ የተገኘ መሆኑን በመጥቀስ በአፈጻጸሙ የእቅዱን 108.5 በመቶ ማሳካት ተችሏል ብለዋል።
የ2018 በጀት ዓመት የተቋሙ ገቢ ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የ27 በመቶ ብልጫ ያለው ነው ተብሏል።
በወሳኝ የባሕር መስመሮች ላይ በርካታ ስጋቶች በተጋረጡበት በዚህ ወቅት ድርጅቱ ፈተናውን ተቋቁሞ ይሄንን ስኬት ማሳካት መቻሉንም ዋና ስራ አስፈጻሚው አክለዋል፡፡ መረጃው ከኢትዮጵያ ባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ የተገኘ ነው።
#EBS
#EBSTVNEWS
#_7696_WN
https://t.me/ebstvnews
www.ebstv.tv